=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
አንድ አይነበሲር ልጅ ከአንድ ህንፃ መወራረጃ ላይ ኮፍያ ይዞ ተቀምጧል፤ ልጁም አይነበሲርነኝ እባካችሁ እርዱኝ የሚል መልዕክት የያዘ ሲሆን ከኮፍያው ያሉት ሳንቲሞች ትንሽ ነበሩ። አንድ ሰው በጎኑ እየተጏዘ እያለ ከኪሱ ሳንቲሞችን አውጥቶ ወደ ኮፍያው አስገባለትና ልጁ የያዘውን መልዕክት አንስቶ ገለበጠና አዲስ ፅሑፍ ፅፎለት በልጁ ጐን የሚያልፉ ሰዎች እንዲያዩት ለእይታ ምቹ በሆነ መልኩ ፅፎ አስቀመጠው።
እናም ኮፍያው መሙላት ጀመረ በርካታ ሰዎችም ለዛ ልጅ ገንዘብ ሰጡት። ከቀትር ሰዓት ብኋላ ያ መልዕክቱን ቀይሮ የፃፈለት ሰውየ እንዴት እንደሆነ ሁኔታውን ሊመለከት መጣ። ልጁም የእግርኮቴውን ተከታትሎ እየተጠራጠረ ጧት መልዕክቱን የቀየርከው አንተነህ? ምነበር የፃፍከው? ሲል ጠየቀው። ሰውየውም ያልከውን ነገር በተለየ መንገድ ነበር የፃፍኩት አለው።
የፃፈውም ዛሬ ቆንጆና ውብ የሆነ ቀን ነው ነገርግን እኔ አላየውም የሚል ነበር። የመጀመሪያውና ሁለተኛው መልዕክት ተመሳሳይ ነገር የሚሉ ይመስላችኋል።
በእርግጥ ሁለቱም መልዕክቶች ልጁ አይነበሲር እንደሆነ ለሰዎች ያስተላልፋሉ። ነገርግን የመጀመሪያው መልዕክት የሚለው ልጁ አይነበሲር ነኝ ነው። ከዚህ ባሻገር ግን ሁለተኛው መልዕክት ሰዎች አይነበሲር ባለመሆናቸው እድለኞች መሆናቸውን የሚያስታውስ መልዕክት ነው። ታዲያ ሁለተኛው መልዕክት የሰዎችን ቀልብ የሚስብ ቢሆን ምን ያስገርማል?
አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል አል-ሉቅማን አንቀፅ 20 ላይ እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 31:20})>=
{20} ፀጋዎቹም ግልፅም ድብቅም ሲሆኑ የሞላችሁ መሆኑን አታዩምን።
አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ሙዕሚኑን አንቀፅ 78 ላይ እንዲህ ይላል:-
{78} እርሱ ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው። ጥቂትን እንጂ አታመሰግኑም።
እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ የአሏህ ፀጋዎች እጅግ በጣም በርካታዎች ናቸውና አስበን እናመስግን።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|